ከሐምሌ ፩ ፳፻፲፩ ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ ፴ ፳፻፲፪ ዓ.ም ለ፲፪ የሚቆይ የስልሳ ዲያቆናት ሥልጠና ተጀመረ።

ሚያዚያ ፱(9) ቀን ፲፱፻፺፯(1997) ዓ.ም. ሁለተኛው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ሲካሄድ በወቅቱ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በበዓሉ ላይ ለተገኙት ተባባሪ አባላት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው የተጀመረውን የማሠልጠኛ ሕንፃ ግንባታ ጎብኝተዋል፡፡

የ፮(6)ኛ ዙር ሠልጣኞች የምረቃ በዓል በሚከበርበት በዓል ዕለት በወቅቱ የሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም ነሐሴ ፳፰(28) ቀን ፲፱፻፺፰(1998) ዓ.ም. የአቡነ ተክለሃይማኖት መቃኞ ቤተክርስቲያን ባርከው ለሠልጣኞችም የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከግንቦት ፳፪(22) ቀን ፲፱፻፺፮(1996) ዓ.ም እስከ ፳፻፫(2003) ዓ.ም በተደረገው መንፈሳዊ የእግር ጉዞ በተገኘው ገቢ ብር ፩ ሚሊዮን ፰ መቶ ፵፮(1,846,000) ሺህ ብር ወጪ ሆኖ የሕንፃው ግንባታ ፺፭(96) በመቶ ተጠናቋል፡፡(ይህ በጥሬ ዕቃና በጉልበትና በእውቀት በነፃ የተደረገውን ድጋፍ አይጨምርም፡፡) ይህ በዚህ እንዳለ የሕንፃ ግንባታው አንደኛ ፎቅ በ፳፻(2000) ዓ.ም ሁለተኛው ፎቅ በ፳፻፰(2008) ዓ.ም በከፊል በመጠናቀቁ በሁለቱም ፎቆች ሥልጠናው በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የማሠልጠኛውን ሕንፃ ለመገንባት ፬ ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ በባለሙያዎች ተገምቶ ነበር፡፡

በ፳፻፰(2008) ዓ.ም ልዩ የሆነ የዲያቆናት ሥልጠና በማዘጋጀት ሥርዓተ ቅዳሴና የወንጌል ትምህርት በጣምራ ለስድስት ወራት እንዲያጠኑ በማድረግ ከዐሥር ሀገረ ስብከት የተላኩ ፵፭(45) ደቀመዛሙረትን አስመርቋል፡፡

የዲያቆናት ሥልጠና ​

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *