በ፳፱ኛው ዙር ክረምት ሥልጠና በ፳ የኅብረተሰቡ ቋንቋ ሊያስተምሩ የሚችሉ፶፯ ደቀመዛሙርት ነሐሴ ፳፮ ፳፻፲፩ ዓ.ም ተመርቅውዋል።

በክረምት ወራት ተጠብቆ በሚሰጠው ሥልጠና የመምህራነ ወንጌልን እጥረት ማስወገድ ስለማይቻል ዓመቱን በሙሉ ማካሄድ እንዲቻል “ኑ እና እዩ” በሚል መሪ ቃል ማኅበሩ ከምእመናን ጋር የተገናኘበት የመጀመሪያው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ተዘጋጅቶ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የከፋ ሸካ ቢንች ማጂ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ የወላይታና ዳሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ በተገኙበት የማሠልጠኛው ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ፤ የአንድነት ኑሮው ከይዞታው በመደበው ፬(4) ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ግንቦት ፳፪(22) ቀን ፲፱፻፺፮(1996) ዓ.ም. ተቀመጠ፡፡

ቀደም ሲል በተጠቀሰው ዕለት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ማሠልጠኛ መታወቂያዋ ቤተ ክርስቲያን ስለሆነች፤ ደቀ መዛሙርት የተግባር ትምህርት የሚያካሂዱበት በጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ ስለዚህ በወቅቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የከንባታ ሐዲያና ጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ፄዴቅ፣ በአፍሪካ ክፍለ ዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ፣ የወለጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ በተገኙበት የቤተ ክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ ሐምሌ ፲፩(11) ቀን ፲፱፻፺፮(1996) ዓ.ም. አስቀመጡ፡፡

፳፱ኛ ዙር ምርቃት​

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *