የእግር ጉዞ

ይህ የእግር ጉዞ ለስልጠናውና ለሕንፃ ግንባታው ገንዘብ የማሰባሰብ ስራውስጥ በቀዳሚነትና በዋናነት የሚጠቀስ የገቢ ምንጭ ማሰባሰቢያ መንገድ ነበር፡፡

በክረምት ወራት ተጠብቆ በሚሰጠው ሥልጠና የመምህራነ ወንጌልን እጥረት ማስወገድ ስለማይቻል ዓመቱን በሙሉ ማካሄድ እንዲቻል “ኑ እና እዩ” በሚል መሪ ቃል ማኅበሩ ከምእመናን ጋር የተገናኘበት የመጀመሪያው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ተዘጋጀ፡፡ ብፁዓን አባቶችና ተባባሪ አባላት በተገኙበት የመጀመሪያው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ግንቦት 22 ቀን 1996 ዓ.ም ተካሂዷል፡፡

በዚህ ወቅት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የከፋ ሸካ ቢንች ማጂ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፤ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣ የወላይታና ዳሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኒቆዲሞስ በተገኙበት የማሠልጠኛው ሕንፃ የመሠረት ድንጋይ ግንቦት 22 ቀን 1996 ዓ.ም. ተቀመጠ፡፡

ሚያዚያ 9 ቀን 1997 ዓ.ም. ሁለተኛው የእግር ጉዞ መርሐ ግብር ሲካሄድ በወቅቱ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳምና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በበዓሉ ላይ ለተገኙት ተባባሪ አባላት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ ሰጥተው የተጀመረውን የማሠልጠኛ ሕንፃ ግንባታ ጎብኝተዋል፡፡

ለማሰልጠኛ የግንባታ ሥራ ገንዘብ ለማሰባሰብ ተባባሪ አባላትን በማስተባበር እስካሁን ድረስ 8 ዙር መንፈሳዊ የእግር ጉዞ ተካሂዷል፡፡

ፍላጎት ካለ የአካል መጉደል የስብከተ ወንጌል ሥራ ከመፈጸም አያግድም ብለው በ1996 በ2ኛው የእግር ጉዞ ላይ አካል ጉዳተኞች ሲሳተፉ የሚያሳይ ምስል ፡፡