መለከት መጽሔት

መምህር ግርማ ከበደ (ገብረእግዚአብሔር) የግል ቤታቸውን ሽጠወ ለማኅበር ካበረከቱት በተጨማሪ መለከትን ስናነሳ በአምደ ሃይማኖት ፣ በነገረ ማርያም ፣ በክብረ ቅዱሳን ፣ በየአብያተክርስቲያናት ታሪክ ፣ በክርስቲያናዊ ሕይወት ፣ በቃለ በረከት ዐምዶች በከባድ ሕመም ውስጥ ሆነው ያበረከቱት ጽሑፎቸ በምዕመናን ልቡና ውስጥ የማይረሱ ዐምዶቸ ናቸው፡፡

መቼ ተጀመረ

ማኅበሩ የተቋቋመበት ዓብይ ዓላማ ለስብከተወንቤል መስፋፋት የልጅነት ድርሻውን ለማበርከት ነው፡፡ በዙህም መሠረት የአንድነት ኑሮው በተጀመረ ነዓመቱ ከኅዳር 21 ቀን 1985 ዓ.ም የመጀመሪያው መጽሔት ታትሞ ለምእመናን ተሠራጨ፡፡ ስለዚህ መለከት መጽሔት በወቅቱ የመጀመሪያዋ ፈር ቀዳጅ ሃይማኖታዊ የማኅበሩ መጽሔት ናት፡፡

ዐላማዎች

 • ምእመናን እምነታቸውን አጽንተው እንዲይዙ የቤተክርስቲያን ሕግ ፣ ሥርዓትና ትውፊት፤
 • የአጽራረ ቤተክርስቲያንን ሂደት እንዲያውቁ ፤
 • በችግር ላይ የሚገኙ ገዳማተ አድባራትና ገዳማትን በማስተዋወቅ ምእመናን እንዲረዷቸው፤
 • በባዕድ አምልኮና ፤ በኃጢአት ተሰነካክለው ያሉ ወገኖቻችን ንስሐ ገብተው ፈጣሪያቸውን እንዲያውቁና ወደ ሥጋ ወደሙ እንዲቀርቡ፤
 • በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙ በጠበል በሌሎችም የቤተክርስቴያኒቱ መንፈሳዊ ጸጋዎ የዳኑተ የምስክርነት ቃላቸውን በማጣት ሌሎችም እንዲጽናኑበትና እንዲጠቀሙበት፤
 • የአብነት ትምህርት ቤቶች አስፈላጊነትና ጠቀሜታ እንዲታወቅ፤
 • ትውልዱ ከቀደሙ አባቶች የሕይወት ተሞክሮ እንዲማር፤

የመጽሔቱ ዓምዶች

የደብዳቤዎች ፣ የክታበ መለከት ፣ የአምደ ሃይማኖት ፣ የነገረ ማርያም ፣ የክብረ ቅዱሳን ፣ የትዕሲት ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ታሪክ፣ የልጆች ፣የወጣቶች የሥርዓተ ቤተክርስቲያን ፣ የልሳነ ካህናት ፣የልሳነ ምእመናን ፣ የክርስቲያናዊ ሕይወት ፣የቃለ በረከት የምዕላደ ጥበብ ፣ የጥያቄዎቻችሁ መልሶች ናቸው፡፡

የኅትመት መጠን

(edited)ከኅዳር ፳፩(21) ቀን ፲፱፻፹፭(1985) ዓ.ም የመጀመሪያው መጽሔት እስከ ኅዳር ፳፻፭(2005) ዓ.ም በ 20 ዓመት ጊዜ ውስጥ አንድ ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ፤ መጽሔቶች በልዑል እግዚአብሔረ ቸርነት ታትመዋል፡፡

ከ፩ኛ ዓመት ቁጥር ፩ እስከ ከ ፲፮ኛ ዓመት ቁጥር ፰ ባሉት ጊዚያት ከታተመው መጽሔት 24546 (ሃያ አራት ሺህ አምስት መቶ አርባ ስድስት) መጽሔቶች ሳይሸጡ በመቅረታቸው ከአሜሪካ፣ ከአቡዳቢ፣ ከእንግሊዝ፣ ከስዊድን እና ከሌሎችም ሥፍራዎች በተላኩልን 17416(አስራሰባት ሺህ አራት መቶ አስራስድስት)ብር ከ ፲ ሺህ ያላነሱ የቆዩ መጽሔቶች የመምህራን ችግር ላለባቸው የገጠሪቱ ቤተክርስቲያን ለማዳረስ ችለናል፡፡ ማህበሩ በየጊዜው ለሚያሰለጥናቸው ደቀመዛሙርት ከየሕትመቱ በነፍስ ወከፍ በነፃ የተሰጠው ተቀንሶ፤ ቀሪው መጽሔት በከፍተኛ ቅናሽ በአንድ ብር ሒሳብ ለጅማ ሐገረስብከት ተሽጧል፡፡ ከ፲፯ኛ ዓመት ቁጥር ፩ ጀምሮ እስከ ፳ኛ ዓመት ቁጥር ሦስት በ ሦስት ዓመት ውስጥ ከታተመው ፻፸፰ መጽሔት መካከል 20,098(ሃያ ሺህ ዘጠና ስምንት ) መጽሔት ሳይሸጥ የዝግጅት ክፍሉን አጣቦ ይገኛል፡፡

ያጋጠሙ ችግሮች

መለከት ከተጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ ችግር አልተለያትም እንደ ችግሮቹ መብዛት መንፈስ ቅዱስ ባያፀናተ ኖሮ ለዛሬው ዕለት መድረስ ባልቻለች ነበር ፡፡

የሚገጥሙንን ችግሮች በየጊዜው ለምእመናን የምንገልጽ በመሆኑ፤ አብዛኛው ለአንባብያን የተሰወረ አይሆንም ብለን እናስባለን፤ ለፉትን እና ብዛት ያላቸውን የውስጥ ፈተናዎችን ትተን እስካሁን ያለተቀረፉት ዋና ዋና ችግሮች የሚከተሉት ናቸው፤

 1. የሕትመት ዋጋ እየናረ መምጣት፡፡
 2. ለመጽሔቱ ቋሚ ደንበኛ በማጣት በከፍተኛ ገንዘብ የታተመው ቃለ እግዚአብሔር ያለ አገልግሎት መቀመጥ፡፡
 3. በመጽሔቱ አለመሸጥ ምክንያት የዝግጅት ክፍሉ የገንዘብ አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ የሥራ ማስኬጃ እጥረት እየገጠመው ስለሆነ፤ ድርጅቱን ከኪሳራ ለመታደግ እና ከመዘጋት ለማዳን ይቻል ዘንድ እርጅና የሌለበት የነፍስ ምግብ የሆነው ቃለ እግዚአብሔር ለረሃብተኞች ይደርስ ዘንድ የተለመደው ትብብራቹ አይለየን፡፡
 4. መጽሔቱ ሲወጣ አበል እየተከፈላቸው የሚያሰራጩ አዟሪዎችን፣ ሰ/ት/ቤቶችን ፣ ማሕበራትን እና ግለሰቦችን በስፋት ማግኘት አለመቻል፡፡
 5. በክፍለ ሃገር የሚገኙ የዱቤ ደንበኞች የወሰዱትን መጽሔት ሸጠው ገንዘቡን በወቅቱ ገቢ አለማድረግ፤ በሰዎች መቀየር ምክንያት ገንዘቡ ገቢ ሳይሆን መቅረት፡፡

ችግሮችን ለመቅረፍ በቢሮው የተወሰዱ እርምጃዎች እና የታቀዱ እቅዶች

 • በጽ/ቤቱ ተርፈው የተቀመጡ መጽሔቶችን በቅናሽ ዋጋ መሸጥ አሻሻጡም
  • 100 እና ከዚያ በላይ መጽሔት በጅምላ ለሚወስዱ በ ብር 1
  • ከ 100 በታች በችርቻሮ ለሚወስዱ በ 1 ብር ከ 50 ሣንቲም
 • በዚህ አጋጣሚ መጽሔቱን ገዝታቹ ለ ገጠሪቴ ቤ/ክርስቲያን አገልግሎት የምትልኩ ግለሰቦች እና መንፈሳዊ ማህበራት በእድሉ እንድትጠቀሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
 • የመጽሔቱን ጥቅም ተረድተው ስራው እንዳይቆም ለሚሹ ምእመናን የዝግጅት ክፍሉን ችግር በግልጽ አሳውቆ የሚሰጡትን የመፍትሄ ሃሳብ መቀበል
 • መነሻ የሚሆን ገንዘብ በብድር የሚሰጡን ወገኖች ብናገኝ በዝግጅት ክፍሉ ቢሮ እና በሌላም ቦታ ሱቅ ተከራይተን ተጨማሪ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን መስራት የምንችልበትን የገቢ ምንጮች ማግኘት

በመጨርሻም ለደንበኞቻችን የመጽሔት ገጽ ብዛት ከፍ እንደምናደርግ እየገለጽን እግዚአብሔር አምላካችን ለዚህ እለት እንዳደረሰን፤ ሃገራችን ኢትዮጵያን እና መላውን ዓለም ጠብቆ ለመጪው አመት በሰላም እንዲያደርሰን ቅዱስ ፈቃዱ ይሁን።

ወስብሐት ለእግዚኣበሔር

ምስጋና

 • መጽሔቷ በ ሃያ አንዱ የማእከሉ ሱቆች እንድትሰራጭ ተረክቦ እና በራሱ መኪና በመውሰድ እና በማሰራጨት እንዲሁም ገንዘቡን ወጪ አደርጎ በአንድ ጊዜ በመክፈል ለሚተባበረን ለማህበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ጸ/ቤት
 • በስርጭቱ ከፍተኛውን አስተፆውን ላደረጉ በ አሜሪካ እና በ አቡዳቢ ለሚገኙ ክርስቲያን ወገኖቻችን
 • ጸሁፍ በማቅረብ መጽሔቷን በማሰራጨት እና በልዩ ልዩ የ ኮምፒዩተር ሙያ ለሚያግዙን በሙሉ
 • በመጽሔቷ አማካኝነት ካርድ የተላከላቸው ማህበሩ ያስጀመረው የሰባክያነ ወንጌል ማሰልጠኛ ለሚረዱ ወገኖቻችን እና ምጽሔቷን ክልብ ለሚደግፉ አንባቢያን ሁሉ በቅዱሳኑ ሥም ምስጋናችንን ማቅረብ እንወዳለን፡፡

ያስጀመረንን ይህን መልካም ስራ እስከ መጨረሻው እንዲያዘልቀን ቸርነቱ የማይለይን አምላክ በ እናቱ ፀሎት ይርዳን፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ ልዩ ልዩ መንፈሳውያን መጻሕፍትንና የመዝሙር ካሴቶችን ተዘጋጅተዋል ከተዘጋጁት እና ለሕተመት ከበቁት ወስጥ

 • ጥንተ አብሶ
 • አንድ ጥያቄ አለኝ
 • ተራደኢው መልአክ
 • ርዕሰ ባሕታዊ
 • መዝሙረ ተዋሕዶ መጽሐፍ ቁጥር ፩ እና ፪
 • የመዝሙር ካሴት ቁጥር ፩ እና ፪

በማሳተምና በማሠራጨት ትምህርተ ወንጌልን ማስፋፋት!!